"የላቀ ትጋት ለትምህርት ጥራትና ለሀገር ብልጽግና!" በሚል መሪ ሀሳብ 31ኛውን ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባኤ አስጀምረናል።
ትምህርት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ትውልድ ላይ ኢንቨስት ማድረግ መሆኑን በመገንዘብ በቁርጠኝነት እና በትጋት እየሰራን ነው።
ሀገር ለመገንባት የታነፀ ትውልድ የሚያስፈልግ በመሆኑ በበጀታችን ከትምህርት ያስቀደምነው ምንም ነገር የለም። ለዚህም በቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራም ከ360 ሺሕ በላይ ህፃናት በቅድመ መደበኛ መርሃ ግብር የተለያዩ ድጋፎችን እንዲያገኙ እና ከ800 ሺሕ በላይ ተማሪዎችን ደግሞ በቀን ሁለት ጊዜ በመመገብ የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት እንዲያገኙ በማድረግ እና ትምህርት ቤቶችን ከአዋኪ ድርጊቶች በማፅዳት ለመማር ማስተማር ምቹ እያደረግን እንገኛለን።
በጉባኤው የ2016 ዓ.ም የትምህርት ስራ ዕቅድ አፈጻጸምን በመገምገም ጠንካራ ጎኖችን አጠናክራችሁ እና አስፍታችሁ እንደምታስቀጥሉ እንዲሁም በትምህርት ስራ ውስጥ ያሉ ድክመቶችን እና ህፀፆችን ነቅሳችሁ በማውጣት ለሚቀጥለው በጀት ዓመት እጥረቱን ለመቅረፍ በትጋት እና በጋራ ርብርብ እንደምትሰሩ ያለኝን እምነት እየገለፅኩ መምህራንን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትምህርት ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንድትወጡ ጥሪ አቀርባለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.