የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ልዑካን ቡድን ከበ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት ልዑካን ቡድን ከበርሊን ከተማ ሚቴ ክፍለ ከተማ ጋር ነሀሴ 20 እና 21, 2016 ዓ.ም ውጤታማ ውይይት አድርጏል።

ውይይቱ በሁለቱ እህትማማች ከተሞች በወሳኝ ትብብር ጉዳዮች በተለይም በጤና፣ በትምህርት እና በአከባቢ ጥበቃ ዙሪያ ዘላቂ ትብብር መፍጠር የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ መሆኑ ተግልፇል::

የበርሊኗ ሚቴ ክፍለ ከተማ ከንቲባ ስተፋኔ ረምልንገር በሁለቱ ከተሞች በጋራ ተጠቃሚነት ዙሪያ አፅንኦት በመስጠት እርስ በእርስ ልምድ መለዋወጥ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል::

ከንቲባዋ የቤርሊኗ ሚቴ ከተማ ልምዷን ለማጋራት ዝግጁ መሆኗን በመግለፅ በአዲስ አበባ ከተማ ለተሰጣቸው ማብራሪያ አመስግነዋል::

የአዲስ አበባ አስተዳደር ከንቲባ ተወካይ ልዑካንን የመሩት ዶ/ር አሻግሬ ገብረወልድ አዲስ አበባ ከተማ ለአለም ከተሞች እድገት የምታጋራው ልዩ ገፅታ እንዳላት ያስታወቁ ሲሆን በተጨማሪም ልዑካን ቡድኑ ከሚቴ ከተማ ለመማር ያለውን ጉጉትም አስታውቀዋል::

ልዑካን ቡድኑ ከሚቴ ከንቲባ ርምልንግር እና ሌሎች ባለስልጣናት ጋር በቻንስለር እና የሀገርቷ ፓርላማ ፊት ለፊት የተተከሉ ዛፎችን በአዲስ አበባ ከተማ ስም ጉብኝቸዋል። 

ልዑኩ በተጨማሪም የጎልማሶች እና መዋዕለ ህፃናት ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማትን ጎብኝቷል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.