ዛሬ ማለዳ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታዉ ሰላም ሰፈር እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በመሬት መንሸራተት በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ ተንዶ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍቅሬ ግዛው ገለፁ።
በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው ሰላም ሰፈር እየተባለ የሚጠራው አካባቢ በመሬት መንሸራተት በአንድ መኖሪያ ቤት ላይ ተንዶ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በአደረጉት ጥረት የስምንት ሰዎች ህይወት ማትረፍ መቻሉ ኮሚሽኑ አስታወቋል።
አደጋዉ የደረሰዉ ሟቾቹና ጉዳት የደረሰባቸዉ ሰዎች በቤታቸዉ እያሉ ሲሆን ህይወታቸዉ ያለፈዉ ሰዎች ሁሉም ወንዶች መሆናቸዉን ተገልጿል ።
በሀገራችን በተለያዩ ክልሎች ተመሳሳይ አደጋዎች እየተከሰቱና ወቅቱ የክረምት ወቅት በመሆኑ የጎርፍ ስጋት እንደሚኖር የአየር ትንበያ ያመላከተ ስለሆነ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ከወዲሁ መልዕክታችን ነው።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.