ዛሬ 2,814 የመስሪያ ቦታዎችን ለከተማችን ኢንተርፕራይዞች እና አንቀሳቃሾች አስተላልፈናል::
ሙሉ በሙሉ መሰረተ ልማት የተሟላላቸው የመስሪያ ቦታዎቹ ለከተማችን ሴቶች፣ ወጣቶች እንዲሁም አካል ጉዳተኛ ለሆኑ ነዋሪዎች የተላለፉ ሲሆን የመስሪያ ቦታዎችን ከመስጠት በተጨማሪ የብድር አቅርቦት፣ በክህሎት የማብቃት እና ክትትል እያደረግን ነው::
የመስሪያ ቦታ የተላለፈላችሁ የከተማችን ነዋሪዎች ቦታዎቹን ለታለመላቸው አላማ ብቻ በማዋል እራሳችሁን፣ ቤተሰባችሁን እና ከተማችሁን እንድትለውጡ አደራ እያልኩ እኛም የሚጠበቅብንን ድጋፍ ማድረጋችንን አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.