የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ስለሰጡን እውቅና...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ስለሰጡን እውቅና እና ስላደረጉልን የምስጋና ፕሮግራም በራሴ ፣ በከተማ አስተዳደሩ አመራር እና ህዝብ ስም አመሰግናለሁ።ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በእርሶ ሃሳብ አመንጪነት እና ቀዳሚ መሪነት ከተማችን አዲስ አበባ እንደስሟ ውብ አበባ ለማድረግ ከለውጡ ማግስት ጀምረን እስከ ኮሪደር ልማት ደረስ በርካታ ጥረቶችን አድርገናል ።በተለይ በኮሪደር ልማት ከሶስት እስከ አራት ወራት ውስጥ የተሰራው ግን የከተማችንን አጠቃላይ ገፅታ የቀየረ ፣አዲስ የስራ ባህልን ያዳበረ እና ለከተማችን ነዋሪዎች ምቹ መኖሪያ እንደትሆን የአደረገ ድንቅ ስራ ነው።

በዚህ በኩል የከተማ አመራር ብቻ ሳይሆን መላው የከተማችን ነዋሪዎች በተለይ በኮሪደር ልማት አከባቢ የሚገኙት ተባብረዋል ፣ ሰርተዋል ፣ኮንትራክተሮችና ኮንሰልታንቾች አብረውን ለነበሩ ሁሉ ዛሬ የቀረበው ምስጋና የሁላችንም እንደሆነ ማስመር እወዳለሁ።

አሁንም ተሰባስበን እና እጅ ለእጅ ተያይዘን የማንቀይረው እና የማንለውጠው ሁኔታ አይኖረም ::

ለህዝባችን ተጠቃሚነት የዛሬው እውቅና የበለጠ ሞራል እና ትጥቅ ሆኖን ዝቅ ብለን የምናገለግል መሆኑን ማረጋገጥ እወዳለሁ ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.