የአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ስኬት የመንግሥት እና የህዝብ ትብብር ውጤት ነው! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር)
በትናንትናው ዕለት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአዲስ አበባ ከተማ አመራሮችና ተግባሩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የፌደራል ተቋማት መሪዎችን በቤተመንግስት በተዘጋጀው መርሃ ግብር በማግኘት እስካሁን በአዲስ አበባ ኮሪደር ልማት ስኬት ዙሪያ ጉልህ ሚና የነበራቸው ግለሰቦችን እና ተቋማትን በመሸለም ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስካሁን ያስመዘገብነው ስኬት የፌዴራል እና የከተማ መስተዳድሩ የጋራ ርብርብ ብቻ ሳይሆን የአዲስ አበባ ነዋሪ ህዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ ውጤት ነው ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሁሉም የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሰጠን እውቅናና ሽልማት አንገታችን ዝቅ አድርገን ለላቀ ውጤት እንድንሰማራ የሚያደርገን ነው ብለዋል።
በሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ህዝባችን በምርጫ 2013 በፀሐይ እና ዝናብ ውስጥ ሆኖ ፓርቲያችን በመምረጥ የሰጠንን ሀላፊነት በአመርቂ ውጤት የሚናሳይበት ነው ያሉት አመራሮቹ 2017 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ለአዲስ አበባ አዲስ የተስፋ ብርሃን ይዞ መምጣቱን ገልፀው የሁለተኛ ዙር ኮሪደር ልማት በላቀ ደረጃ ጀምሮ ለመጨረስ ዝግጅት መጠናቀቁን አረጋግጠዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.