ንግድ ቢሮ ፀረ-ሙስና ትግሉን ከውስጥ መጀመሩን ገለፀ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ፀረ-ሙስና ትግሉን ከውስጥ መጀመሩን ገለፀ፡፡
በዛሬው ዕለት ለቢሮው የኢንፎርሜሽን ፣ ኮሙኒኬሽንና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የንገድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለፁት የኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎትን ከአዋጅና መመሪያ ውጪ አገልግሎት በሰጡና ተመሳስሎ በተዘጋጀ ቲተርና ፊርማ አዲስ ንግድ ፈቃድ በሰጡ 7 ባለሙያዎቹ ላይ እርምጃ መውሰድ ተገልፃል፡፡
የቢሮው የኢንፎርሜሽን፣ ኮሙኒኬሽንና ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ገመቺስ መንግስቱ እንደገለፁት ከኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በስራ ባልደረባቸው አካውንትና የይለፍ ቃል በመግባት ተመሳስሎ በተዘጋጀ ቲተርና ፊርማ አዲስ ንግድ ፈቃድ የሰጡ 4 ባለሙያዎችና አንድ ለጊዜው በተሰወረ በድምሩ 5 ባለሙዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ይገኛል ብለውናል፡፡
የቢሮው የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሚሊዮን ካሳ በበኩላቸው የአክሲዮን ማህበር ካፒታል ለማሻሻል መሟላት ያለባቸው ሰነዶች ሳይሟሉ እንዲሁም ለንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ሲስተም የተሳሳተ ሰነድ በማስገባት የአክሲዮን ማህበሩን ካፒታል ከ600 ሺህ ወደ 212 ሚሊዮን አሳድጓል የተባለ አንድ ባለሙያ ተጠርጥሮ ጉዳዩ እእንዲጣራ እየተደረገ ይገኛል፡፡
በተመሳሳይም ቢሮው ባልተሰጠው ስልጣን የባንክ ስራ ፈቃድ የሰጠ አንድ ባለሙያ እንዲታገድ የተደረገ ሲሆን ጉዳዩ ከተጠራ በኃላ ተገቢው እርምጃ እንደሚወሰድም ነግረውናል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ሌብነትና ብልሹ አሰራር ላይ የተጀመረ ትግል በማጠናከር መሰረታዊ ለውጥ ማምጣት የ2017 በጀት ዓመት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነ ማስቀመጣቸው ይታወሳል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.