ሰራተኛ መስለው የኮሪደር ልማት ግብዓቶችን የሰረቁ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፦
ዛሬ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት
አፍሪካ ፓርክ አከባቢ ሰራተኛ መስለው በመግባት የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ግብዓቶችን የሰረቁ ግለሰቦች እጅ ከፍንጅ ተይዘው ፖሊስ ምርመራ እያደረገባቸው ይገኛል።
በየትኛውም ቦታ የሚሰራው የመሰረተ ልማት ስራ ለመላው ህዝብ ጥቅም በመሆኑ ነዋሪ ህዝባችን በተለመደው መልኩ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር በመተባበር የጋራ በሆኑ ልማቶቻችን ላይ ጥፋት የሚያደርሱትን ግለሰቦች እና ቡድኖች የማጋለጥ ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን ያቀርባል።
ከዚህ አንፃር የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ እያደረገ ላለው የማይነጥፍ ትብብር አስተዳደሩ ያመሰግናል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.