ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካን እሳቤዎች ዕውን ለማድረግ ቁርጠኛ ናት፡- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
ኢትዮጵያ የፓን አፍሪካን እሳቤዎች ዕውን ለማድረግ ቁርጠኛ ናት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ዛሬ በአዲስ አበባ በተጀመረው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ላይ መገኘታቸውን የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ለአፍሪካ የከተማ ልማት ችግሮች አህጉራዊ፣ የፖሊሲ እና ስልታዊ መፍትሄዎች የሚመክረውን ይህን መድረክ ሀገራችን እንደ መልካም ዕድልና አፍሪካዊ ሃላፊነት አድርጋ ትወስዳዋለች ብለዋል፡፡
ይህ ፎረም በአፍሪካ ዕድገት ላይ እንድናሰላስል፣ ሀሳቦችን እንድንለዋወጥ እና በአህጉራችን ውስጥ ዘላቂ፣ አካታች እና የበለፀጉ ከተሞችን ወደፊት ለመፍጠር ዕድል ይፈጥርልናል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡
የበለጸገች አፍሪካን ለመገንባት የጋራ ጥንካሬዎቻችንን መጠቀም አለብን ያሉት አቶ ተመስገን፤ ለዘመናችን ፈተናዎች ከተለመዱት ምላሾች በተለየ ከፖለቲካዊ ስልቶቻችን ጋር የሚጣጣሙ አፍሪካዊ መፍትሄዎችን መፍጠር ይገባናል ብለዋል፡፡
EBC
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.