ከመላው አፍሪካ እና ሌሎች ሀገራት የመጡ ሚንስት...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ከመላው አፍሪካ እና ሌሎች ሀገራት የመጡ ሚንስትሮችን ፣ከንቲባዎችን፣ የዘርፉ ተመራማሪዎችን እንዲሁም ሌሎች የዘርፉ ባለድርሻ አካላትን ወደ ሁለተኛ ከተማችሁ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለን ተቀብለናቸዋል::ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የአፍሪካ ከተሞች ያላቸውን እምቅ አቅም መጠቀም በሚችሉበት መንገድ ላይ በሚመክረው በዚህ መድረክ አዲስ አበባ ነዋርዎቿን በማሳተፍ ለኑሮ ምቹ፣ አረንጓዴ እና ደህንነቷ የተጠበቀ የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ የሰራናቸውን ስራዎች ለአፍሪካ ፎረም ተሳታፊዎች አቅርበናል::

መጪው ጊዜ በዋነኛነት በአፍሪካ ለሚፈጠረው ፈጣን የከተሞች እድገት እና መስፋፋት ከወዲሁ ዝግጅት ለማድረግ የአፍሪካ ከተሞች ከምንጊዜውም በላይ ተቀራርበው ልምድ እየተለዋወጡ መስራት ይጠበቅባቸዋል::

የአፍሪካ ከተሞች ለውጥ ለአህጉሪቱ ኢኮኖሚ፣ ልማት እና ከዚያ በላይ ሞተር ሆኖ የሚያገለግል ሲሆን የከተሞችን አቅም ለመጠቀም አመራር የማይተካ ሚና የሚጫወት በመሆኑ መሰል የውይይት መድረኮች ልምድ ለመለዋወጥና በትብብር ለመስራት  ትልቅ ሚና የሚጫወት ይሆናል::

ከተለያዩ የአለም እና የአፍሪካ ሃገራት በዚህ መድረክ ላይ ለመሳተፍ የመጣችሁ እንግዶቻችን ሁለተኛ መዲናችሁ በሆነችው አዲስ አበባ የሚኖራችሁ ቆይታ ፍፁም ስኬታማ እና ያማረ እንዲሆን እመኛለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.