ዛሬ ጠዋት በዓድዋ ድል መታሰቢያ የተጀመረው የአ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዛሬ ጠዋት በዓድዋ ድል መታሰቢያ የተጀመረው የአፍሪካ ከተሞች ፎረም ከሰዓት በተለያዩ አዳራሾች በተለያዩ ውይይቶች ቀጥሎ ውሏል።

ከአህጉሪቱ የተለያዩ ከተሞች የተውጣጡ ከንቲባዎችን፣ ኤክስፐርቶችን እና ዲፕሎማቶችን በማገናኘት "በአህጉራችን ባለው የከተማ ልማት ላይ እንነጋገር" በሚል ውይይት ተደርጏል። 

ውይይቱን የከፈቱት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይ ሊያስከትል የሚችለውን ችግር በአግባቡ መቆጣጠር ከተቻለ የከተሞች መስፋፋት ለከተማ እድገትና ለነዋሪዎች ትልቅ አስተዋዖ እንዳለው በመድረኩ ላይ የተናገሩ ሲሆን የከተማ ልማትን በመቅረጽ ረገድ ከንቲባዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሊሰጡባቸው የሚገቡ ወሳኝ ጉዳዮችንም አንስተዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.