“አዲስ ዓመት ስንቀበል ለአዲስ ለውጥ፣ ለአዲስ ፈጠራና ለአዲስ ትጋት ዝግጁ መሆን አለብን፡፡ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በተለያዩ ስያሜዎች የሚከበረውን የጳግሜ ቀናት ጳጉሜን 1/3016 የመሻገር ቀን "የመሻገር ጥሪቶች፤ የአዲስ ብርሃን ወረቶች" በሚል መሪ ቃል በልዩ ልዩ ሁነቶች እያከበረ ይገኛል፡፡ በዚህም የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች እና የከተማ ግብርና ውጤት አቅራቢዎች የተሳተፉበት ከተማ አቀፍ ኤግዚቢሽንና ባዛር በመስቀል አደባባይ ተከፍቷል፡፡
ኤግዚቢሽንና ባዛሩን የከፈቱት አዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት በአለፉት ዓመታት በሀገር ደረጃ ወደ አዲስ ዘመን መሸጋገሪያ የሆነችውን የጳጉሜ ወርን ሀገራዊ አብሮነትንና መተሳሰብን በሚያዳብር መልኩ በተለያዩ ስያሜዎች ሲከበር እንደቆየ ገልጸው አዲስ ዓመት ስንቀበል ለአዲስ ለውጥ፣ ለአዲስ ፈጠራና ለአዲስ ትጋት ዝግጁ በመሆን አዲስ ራዕይ ሰንቀን የምንቀበለው ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
አቶ ጃንጥራር አከክለዉም በኤግዚቢሽንና ባዛሩ አምራቹና ሸማቹን የሚያገናኝ ከመሆኑም ባሻገር ሀገር በቀል ምርቶችን የሚያገኙበት ስለሆነ የከተማችን ነዋሪዎች ለአዲሱ ዓመት የበዓል ዝግጀት የሚሆኑ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ወደ በሚቀርበው አካባቢ በመሄድ ምርቶቹን እንዲሸምቱ ጠቁመዋል፡፡
በመጨረሻም ሁሉም የጳጉሜ ቀናት በልዩ ለልዩ ፕሮግራሞች እንደሚከበር ገልጸው አዲሱ ዓመት ከድህነት ወደ ብልፅግና በአብሮነት የምንሻገርበት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ምክትል ከንቲባው ገልጸዋል፡፡
በኤግዚቢሽን እና ባዛሩ የከተማዋ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.