አዲስ አበባ እያሳየች ያለውን የከተማ ልማት እመርታ ለውጥ ለአፍሪካዊያን የጉባኤ ተሳታፊዎች በተምሳሌትነት የሚጠቀስ ነው ተባለ፡፡
የመጀመሪያው የአፍሪካ የከተሞች ፎረም “ዘላቂ የከተሞች ልማት ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳ 2063” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
በአዲስ አበባ እየተመዘገበ ያለው ፈጣን እድገት ለሌሎች የአፍሪካ ከተሞች በተምሳሌትነት የሚጠቀስ ነው ሲሉ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ተወካዮች ተናግረዋል ።
ከርዋንዳ ኪጋሊ በመወከል በፎረሙ እየተሳተፉ የሚገኙት መኩዋኔ ቲዩኒዜማ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ በኢኮኖሚያዊ መነቃቃት ፣ በህዝቦቿ ቤተሰባዊነት እና በመሰረተ ልማት ለውጥ ምን ያክል እንደተለወጠች ቀድሞውንም ውብ ከሆነችው የኔዋ ኪጋሊ እየቀደመች መሆኑን አይቻለው ሲሉ ተናግረዋል።
ከጋምቢያ የመጡት የፎረሙ ተሳታፊ ፋማራ ኩዊቴ በበኩላቸው ተምሳሌታዊና በፍጥነት እየተለወጠ ያለን የአዲስ አበባን ገፅታን መለወጥ ሳይ ሂደቱ በዕጅጉ የሚገባው ነው፤ አዲስ አበባ በርግጥም የአፍሪካ እንዲሁም የአለም ዲፕሎማቶች መቀመጫ ናት፤ አሁን እያሳየች ያለው ለውጥና መሻሻል የሚጠበቅና የሚገባትም ጭምር ነው፡፡ መንግስትም ትልቅ አሻራ እያኖረ እና ለልማት ሥራዎችና ለህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች የተሰጠው ትኩረት ቀልብ የሚስብ መሆኑን አንስተዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.