ሪፎርም ለላቀ አገልግሎት!
በሪፎርም ጀምረን ትልቅ ውጤት ካስመዘገብንባቸው ስራዎች አንዱ የሆነው እና ለረዥም ጊዜያት የህዝባችን የቅሬታ ምንጭ የነበረው የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት በ119 ወረዳዎች ዲጂታላዝ አድርገን የዜጎቻችንን እንግልት መቀነስ የሚያስችል ደረጃ ላይ በማምጣታችን በጣም ደስ ብሎናል::
የሪፎርማችን ውጤታማነት የሚለካው ለህዝባችን ፍትሀዊ አገልግሎት በመስጠት በመሆኑ አገልግሎትን የሚያቀላጥፍ እና የህዝቡን እንግልት የሚቀንስ የሪፎርም ስራዎችን ከሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት በተጨማሪ በሁሉም ተቋሞቻችን ላይ በከፍተኛ ተነሳሽነት በመስራት ላይ እንገኛለን::
ዛሬ ያስመረቅነው የዲጂታላይዜሽን ስራ ከዋና መስርያ ቤት እስከ ወረዳ ያለውን የቴክኖሎጂ መስመር በአዲስ አሰራር የቀየረ፣ 19ኙም የተቋሙ ጽ/ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጥ በቀጥታ በካሜራ ቁጥጥር የሚደረግበት (Command Center) ያቀፈ፣ በአይነቱ በሃገራችን የመጀመርያ የሆኑ የዘርፉ መፍትሄዎችን የያዘ እንዲሁም በከተማችን የሚሰጠውን አገልግሎት ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ነው::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.