በዛሬው የሪፎርም ቀን 24ኛ ዙር የአዲስ አበባ ፖሊስ መኮንኖችን መርቀን ወደ ስራ አስገብተናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የሪፎርም አንዱ መሰርት የተጣለው በጸጥታ ሃይላችን ውስጥ መሆኑ ይታወቃል። የአዲስ አበባ ፖሊስም ሪፎርም እያካሄደ የከተማችንን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ተግባሩን በትጋት እና በብቃት በመወጣት ላይ ይገኛል።
የዛሬ ተመራቂዎች ስልጠና እና ምርቃትም በሪፎርሙ የጀመርነው ፖሊስን በስነ ልቦና፣ በቴክኒክ፣ በታክቲክ እና በሰው ሃይል የማጠናከር ተግባር አካል ሲሆን የህብረተሰቡን አጋርነት በልኩ የሚጠቀም የፖሊስ ሃይል ሀገር ያሻግራልና በከተማችን የጀመርናቸው ስራዎችን እንዲሁም እቅዶቻችንን እውን ለማድረግ ሀላፊነቱን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ ከራሱ ጥቅምና ፍላጎት ይልቅ የህዝቡን ፍላጎትና ጥቅም የሚያስቀድም፣ የአገልጋይነት ስብዕና የተላበሰ የፀጥታ ሐይል በመሆን ህዝባችሁን ያለአንዳች አድልዎ በታማኝነት እና በቅንነት እንድታገለግሉ አደራ እላለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.