ዘመናዊ ያልሆኑ አሰራሮችን በማዘመን የማህበረሰባ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ዘመናዊ ያልሆኑ አሰራሮችን በማዘመን የማህበረሰባችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል፡፡አቶ ሞገስ ባልቻ የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት በአዲስ መልክ የታደሰውን የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት መርቀዋል፡፡

ጳጉሜ ሁለት የኢትዮጵያ የሪፎርም ቀን እንዲሆን በማድረግ የተጀመረው ሪፎርማችን እንዲቀጥል ማድረግ ይገባናል ያልሉት የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ የቆዩ አሰራሮችን በማስተካከል ወደ ዘመናዊነት የመቀየር ሥራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ 

ፓርቲያችን ብልፅግና ለህዝብ አገልግሎት መሻሻል በመንግስት በኩል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑንን የሚያሳይ ተግባር ላይ መሆናችንን በዛሬው ዕለት ማረጋገጥ ችለናል ብለዋል አቶ ሞገስ፡፡

አራዳ ክፍለ ከተማ እየለማች ያለች በመሆኑ አገልግሎት አሰጣጣችንም ያልዘመነበት ሁኔታን የመለወጥ ስራው ከሁሉም በፊት ትኩረት ሊደረግበት የሚገባ ነው ሲሉ አቶ ሞገስ ባልቻ አክለው ገልፀዋል፡፡

አቶ ጌታሁን አበራ የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሲሆኑ በክፍለ ከተማችን በዛሬው ዕለት የጳጉሜ 2 ቀንን ስናከብር የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ መለወጥ ያለበትን ያልዘመነ አሰራር ለመለወጥ ታሳቢ በማድረግ ነው ብለዋል፡፡ 


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.