"በአዲስ ምዕራፍ በአዲስ አስተሳሰብና በአዲስ መንፈስ ለህዝባችን ፈጣን ተደራሽና ጥራት ያለው አገልግሎት ለማቅረብ በትኩረት እየሰራን ነው" ዶ/ር ጀማሉ ጀንበር
በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 5 አስተዳደር "የሪፎርም ቀንን" ምክንያት በማድረግ በቴክኖሎጅ የዘመነ የሲቪል ምዝገባ አገልግሎት መስጫ ተቋም ተመረቀ
በምርቃት ፕሮግራሙ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀንበር(ዶ/ር) እንደተናገሩት የቀድሞው ወሳኝ ኩነት የአሁኑ የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ባለፍት ዓመታት ለብልሹ አሰራር የተጋለጠና የአሰራር ክፍተቶች የነበሩበት ተቋም ነበረ ብለው አሁን ላይ ተቋሙን ሪፎርም በማድረግና የአሰራር ክፍተቶችን በመቅረፍ ፈጣን ውጤታማና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው አገልግሎት መስጠት እንዲችል ተደርጓል በቀጣይም ተቋሙ የበለጠ ውጤታማ አገልግሎት እንዲሰጥ የማዘመን ስራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ ተቋም በርካታ ህ/ሰብ በተደጋጋሚ ለአገልግሎት የሚመጣበት ተቋም በመሆኑ አገልግሎት አሰጣጡን የላቀ በማድረግ በውጤታማ አገልግሎት አሰጣጥ ለሌሎች ተቋማት አርዕያ እንዲሆንም ይሰራል ብለዋል።
የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ እንደተናገሩት በ2016 በጀት ዓመት ባደረግነው ግምገማ የመልካም አስተዳደር ስራዎቻችን ላይ የሚቀረን እንዳለ ገምግመናል በመሆኑም በ2017 በጀት ዓመት ህ/ሰቡን በታማኝነትና በታታሪነት ለማገልገል ተዘጋጅተናል ብለው ለዚህም ስኬት የተቋማትን አገልግሎት እያዘመን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።
ማገልገል ክብር በመሆኑ ያለእረፍት ህ/ሰባችንን በማገልገል በትኩረት እንሰራለን ያሉት ወ/ሮ አበባ ለዚህም ሁሉም የየድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.