በመዲናዋ ጳጉሜ 2 የሪፎርም ቀን ከማዕከል እስከ ወረዳ ባሉ የመንግስት ተቋማት ለህብረተሰቡ አገልግሎት በመስጠት ሲከናወን ውሏል።
በአዲስ አበባ ከተማ ጻጉሜ 2 የሪፎርም ቀን “ሪፎርም ለላቀ ልማት!” በሚል መሪ ቃል ከማዕከል እስከ ወረዳ ባሉ የመንግስት ተቋማት ለህብረተሰቡ አገልግሎት በመስጠት ሲከናወን ውሏል።።
በዕለቱ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ቀኑን አስመልክተዉ በአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በመገኘት እንደተናገሩት በተለይም ከለውጡ ወዲህ አዳዲስ የሪፎርም ሥራዎችን ተግባራዊ ለማድረግ በተከናወኑ ጥረቶች በርካታ ሥራዎች መሠራታቸውን እና በዚህም ከፍተኛ ውጤት መገኘቱን ገልፀዉ ዜጎች የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመላመድ እና በመጠቀም አገልግሎታቸውን በተሳለጠ አካሄድ ማግኘት እንደሚኖርባቸውም አሳስበዋል።
ባለሙያዎችም የዘመኑን ቴክኖሎጂ በብቃት በመታጠቅ አገልግሎት አሰጣጣቸውን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ እና የዜጎችን እንግልት በሚያስቀር መልኩ መከወን እንዳለባቸውም ከንቲባ አዳነች አመልክተዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ በማዕከል፣በ11ዱም ክፍለ ከተሞች እና በሁሉም ወረዳዎች የመንግስት ተቋማት ለህብረተሰቡ ቀኑን ሙሉ አገልግሎት በመስጠት እያከበሩ ሲሆን የሪፎሙ ውጤታማነት የሚለካው ለህዝባችን ፍትሀዊ አገልግሎት በመስጠት በመሆኑ አገልግሎትን የሚያቀላጥፍ እና የህዝቡን እንግልት የሚቀንስ የሪፎርም ስራዎችን ከሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት በተጨማሪ በሁሉም ተቋሞቻችን ላይ ተነሳሽነት መፈጠሩን ይህም የበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እና የሁሉም ሀላፊነት መሆን እንዳለበት ገልፀዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.