ሉዓላዊነታችንን ጠብቀን መኖራችን ያኮራናል። የግ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ሉዓላዊነታችንን ጠብቀን መኖራችን ያኮራናል። የግዛት ሉዓላዊነት ብቻውን እንደማይቆም ግን ተረድተናል። ሉዓላዊነት ሁለንተናዊ መሆን አለበት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ

የምግብ ሉዓላዊነት፣ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ፣ የበጀት ሉዓላዊነት፣ ታላቁን የሀገር ሉዓላዊነት በጽናት የሚያቆሙ ናቸው። እነዚህን የሉዓላዊነት ዘርፎች ለማስከበር አዲሱ ዓይነት ዐርበኝነት ያስፈልገናል። የብሔራዊነት ዐርበኝነት። 

የብሔራዊነት ዐርበኝነት በተሠማራንበት መስክ ሁሉ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ለማስከበር የጊዜ፣ የዕውቀት ፣ የገንዘብና የጉልበት መሥዋዕትነትን መክፈል ነው። ሀገር በልጆቿ ትገነባለች ትጠበቃለችም።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.