ዛሬ ጷጉሜ 3 በሉአላዊነት ቀን "ህብር ለሁለንተናዊ ሉአላዊነት " በሚል መሪ ቃል በለሊት ተነስቶ በነቂስ ከወጣዉ ከከተማችን ነዋሪ እና የፀጥታ ሀይላችን ጋር በመስቀል አደባባይ በድምቀት አክብረናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ሉዓላዊነት በደም በአጥንት የፀናች እና ከአባቶች የተረከብ ናት ሉዓላዊነት ሀገር ናት !
ለኢትዮጵያ !
ለሀገራችን !
የደም መሥዋዕትነት ከፍለን ያስገኘነውን ሉዓላዊነት ላባችንን አፍስሰን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን ለማስከበር ዛሬም ጠንክረን መስራት ይጠበቅብናል !!
ሉአላዊነትን ማረጋገጥ በሀሳብ መግባባት ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የሀላፊነት ስሜትና ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ እንደሀገር ነጻነታችንን የሚፈታተኑ ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታዎችን በመከታተልና በማምከን ሂደት ውስጥ የእያንዳንዳችንን የነቃ ተሳትፎ ይጠይቃል፡፡
የከተማችን ነዋሪዎች፣ የሀገራችን የፀጥታ ሀይሎች በፈተናዎች ሁሉ አልፋችሁ ለሀገራችን የኢኮኖሚ ሉአላዊት ለምታደርጉት ተጋድሎ እና ጥረት ኢትዮጵያ ሁሌም ታመሰግናችኋለች !!
ፈጠሪ ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿን ይባርክ !!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.