"ሀገራችን ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷ ሳይደፈር በነፃነት የኖረች ሃገር ናት" ከንቲባ አዳነች አቤቤ
ጳጉሜ 3 የሉዐላዊነት ቀን "ኅብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት!" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በደመቀ ሥነ-ስርዓት ተከብራል።
በእለቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሀገራችን ኢትዮጵያ በልጆቿ ደምና አጥንት ሉዓላዊነቷ ሳይደፈር በነፃነት የኖረች ሃገር ናት ብለዋል።
ሀገር በነፃነት ተከብራ ስትኖር ልማታችን ይቀጥላል ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለሃገራችን ሉዓዋላዊነት እና ክብር ከውጪ የሚቃጣባት ጥቃት በልጆቿ ደምና አጥንት ያለአዳች ማመንታት ሉዓላዊነቷ ሲከበር መቆየቱን ተናግረዋል።
አያይዘውም የሀገራችን ነፃነት እና ሉዓላዊነት ለማስከበር ከተለያዩ ግጭቶች ሃገራችን በማስከበር ብቻ አለመሆኑን የጠቆሙት ከንቲባ የሀገራችን ሉዐላዊነት የተሟላ እንዲሆን በኢኮኖሚ እራሷን የቻለችና የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመገንባት ሁላችንም በትጋት በመረባረብ መስራት እንደሚጠበቅብን ጭምር አሳስበዋል።
እስከዛሬ በርካታ እዳወችን ስንከፍል ቆይተናል ከዚህ በኃላ ለትውልዱ እዳ ሳይሆን ምዳን ለማስተላለፍ መስራት እንደምንችል በርካታ ማሳያ የሆኑ ስራወችን በመስራት ውጤታማ መሆን መቻላቸውንም ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አሰተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው በለውጡ መንግስታችን ሃገራችን ኢትዮጵያዊ እና ከተማችን አዲስ አበባን መምራት ከጀመረበት ጀምሮ ባፉት አመታት የአገራችን ሉአላዊነት ከመጠበቅ አኳያ የውጭ እና የውስጥ ጫናዎችን በመቋቋም በርካታ ድሎች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት አደጋ ላይ ለመጣል አቅደው የሚሰሩ ሀይሎች እየተጉ ያሉበት በመሆኑ የሀገራችን እና የአካቢያችን ሰላም እንዚህ ቀደሙ ለመጠበቅ ከፀጥታ አካላት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘንና ተቀናጅተን መስራታችንን የበለጠ አጠናክረን መጠበቅ አለብን ሲሉም ወይዘሮ ሊዲያ ግርማ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.