"ህብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተወጣጡ ነዋሪዎች እና የፀጥታ አካላት ጋር "ህብር ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ ቃል የፓናል ውይይት ተካሄደ። ፓናል ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በዚህን ወቅት እንደተናገሩት ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የአገሪቱን ሉአላዊነት ከመጠበቅ አኳያ የውጭ እና የውስጥ ጫናዎችን በመቋቋም በርካታ ድሎች መመዝገባቸውን አመላክተዋል፡፡
በተለይም የታላቁ ህዳሴ ግድብን ግንባታ ለማስተጓጎል እና በዚህም ሉአላዊነታችንን ለመዳፈር ሌት ተቀን ተደክሟል አሁን እየተደከመ ነው ብለዋል፡፡
የቢሮ ኃላፊዋ አክለውም የስልጣን ምንጭ የህዝብ ድምጽ መሆኑን የዘነጉ እና ስልጣን በአፈሙዝ ለመንጠቅ የሚሞክሩ ጽንፈኛ ሀይሎች የአገራችንን አንድነት ለመናድ ሞክረው እንዳል
ተሳካላቸው ወ/ሮ ሊዲያ ጠቅሰዋል፡፡
በዚህም ለሀገራቸው ሰላም እና ደህንነት መስዕዋትነት ህይወታቸውን እየሰው ላሉ የጸጥታ ኃይሎች ክብርና ምስጋና ይገባዋል ብለዋል፡፡
ለፓናል ውይይቱ መነሻ ሀሳብ ሰነድ ያቀረቡት የኢ-ፈደሪ መከላከያ ሚኒስቴር ባልደረባ ኮሎኔል አቡሽ ገብሬ ሲሆኑ የአፍሪካ ህብረት ቻርተር፣ የኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀጽ 8፣ሉዓላዊነት እና የፀጥታ ሃይሎችን ሚና እንዲሁም ሰለቀጠናዊ የፀጥታ ሁኔታ በሰፊው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
መድረኩን የመሩት የቢሮው ሃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊድያ ግርማ፣የኢፈደሪ መከላከያ ሚኒስቴር ባልደረባ ኮሎኔል አቡሽ ገብሬ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርገው እንደተናገሩት የውጭ ሐይሎች በሀገር ውስጥ ክፍተት አለ ብለው ባሰቡ ወቅት ሁሉ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለመዳፈር ይሞክራሉ ፣ይህንን ድርጊት እንደ ቀደምት አባቶቻችን ያለም
ንም ልዩነት መመከት አለብን ብለዋል ።
በመጨረሻም የፓናል ውይይቱ ተሳተፊዎች አሁን ያለንበት ጊዜ የዜጎችን አንድነት እና ሕብረት የሚያስፈልግበት ወቅት ስለሆነ አንድ እንሁን በማለት የአንድነት ቃል መገለጫ የሆነውን ቃለ-መሃላ ፈፅመዋል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.