አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ክፍለ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ክፍለከተሞች የተገነቡ 837 መኖሪያ ቤቶችን ለአቅመ ደካሞች እና ለሀገር ባለውለታ ነዋሪዎቻችን አስተላልፈናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብተው ለነዋሪዎች ከተላለፉ ቤቶች ውስጥ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በየካ ክፍለ ከተማ 54 ቤቶችን የገነባ ሲሆን ለዚህም ክብርት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚልን አመሰግናለሁ። እንዲሁም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለከተማ በተለያዩ ባለሀብቶች 108 ቤቶች፣ በአራዳ ክፍለከተማ በአብዱለጢፍ ዑመር ፋውንዴሽን (አሚባራ ግሩፕ) 32 ቤቶች ተገንብተዋል። ሁሉንም ቤቶች ለነዋሪዎች አስተላልፈናል።

ነዋሪዎች አዲስ ዓመትን በአዲስ ተስፋ እንዲጀምሩ ትልቅ አስተዋፅዖ ያበረከታችሁ ተቋማት እና የከተማችን ልበ ቀና ባለሃብቶችን በራሴ፣ በከተማ አስተዳደሩ እና በነዋሪዎቹ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.