ዛሬ ማለዳ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ከ500 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች፣ የሀገር ባለውለታዎች እና በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ የመንግስት ሰራተኞች ማዕድ አጋርተናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የምናጋራው ማዕድ ብቻ ሳይሆን ለወገኖቻችን ያለንን ፍቅርና አክብሮት ጭምር ሲሆን ማዕድ ማጋራቱ ወገኖቻችን በዓሉን በደስታ እንዲያከብሩት የሚረዳ ነው።
የመንግስትን የሰው ተኮር ፖሊሲ አቅጣጫ እና ጥሪ በመቀበል ሰርተው ካገኙት ለወገኖቻቸው ማካፈልን ባሕል ላደረጉ የከተማችን ልበ ቀና ባለሀብቶች እና በጎ ፈቃደኞች እንደሁልጊዜው ሁሉ መስጠት አያጎድልምና ለወገኖቻችሁ ለምታደርጉት በጎነት ሁሉ በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.