ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን በሰጡን ኃላፊነት መሰረት ዛሬ በጎንደር ከተማ ተገኝተን በፍጥነት ያስጀመርነው የኮሪደር ልማት ስራ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
የኮሪደር ልማት ስራው 12 ኪ.ሜ ርዝመት አለው። በዋነኛነት ከኤርፖርት እስከ መሃል ከተማ ፒያሳ፣ ፋሲል ግንብ ዙሪያን እንዲሁም ፒያሳ አካባቢ የማደስ ስራን ያካተተ ሲሆን የህዝቡ ተባባሪነት ከፍተኛ በመሆኑ በፍጥነት እየተሰራ ይገኛል።
የጎንደር ከተማ ጥንታዊ እና ታሪካዊ ከተማ እንደመሆኗ በኮሪደር ልማት ስራችን ህንፃዎችን እና ታሪካዊ ቦታዎችን በማደስ የቱሪስት መስህብነቷ ይበልጥ እንዲጨምር የምንሰራ ይሆናል።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.