ሰርተው ካገኙት ለወገኖቻቸው በፍቅር ላካፈሉ ልበ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ሰርተው ካገኙት ለወገኖቻቸው በፍቅር ላካፈሉ ልበ ቀና ባለሀብቶች እና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች እውቅና እና ሽልማት ሰጥተን አመስግነናቸዋል::ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባችን ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት መዲና እንድትሆን ያደረግነው ጥረትና ልፋት ፍሬ አፍርቶ በእናንተ ቅንነት እና በጎነት የበርካቶችን እምባ አብሰን የመኖር ተስፋቸውንም አለምልመናል::

ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከ35 ሺሕ በላይ ቤቶችን እንዲሁም ባለፈው አንድ ዓመት ደግሞ 7,567 ቤቶችን ገንብተን ለአቅመ ደካሞች በማስተላለፍ ኑሮአቸውን አቃንተናል::

 በ2016 በጀት ዓመት ብቻ 12 ቢሊዮን ብር በበጎ ፈቃድ የማስተባበር እንዲሁም በዚህ ዓመት ብቻ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች ማዕድ በማጋራት ለወገኖቻችን አለኝታነታችንን አሳይተናል

መስጠት አያጎድልም በማለት በቅንነት ለወገን የተረፈ የበጎ ፈቃድ ስራ ላይ የተሳተፋችሁ ልበ ቀና ባለሀብቶች እንዲሁም ያስተባበራችሁና የመራችሁ በየደረጃው ያላችሁ አመራሮች እምባቸው በታበሰ እና ኑሯቸው በተቃና ዜጎቻች እንዲሁም በራሴ ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ::

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.