ዛሬ የነገ ቀንን “የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፋት “ብለን ትኩረት ተነፍገው ለነበሩ ትኩረት እና ክብር እየሰጠን በበርካታ ዝግጅቶች እያከበርን ነው። ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በብርሃን የአይነ ስውራን አዳሪ ትምህርት ቤት ከክብርት ቀዳማዊት እመቤት ጋር በመሆን አብረናቸው ቆይታ አድርገን እንኳን አደረሳችሁ ብለን ቀጣዩ የትምህርት ዘመን ብረሃናማ እና የተሳካ እንዲሆንላቸው ተመኝተናል።
እንዲሁም በነገዋ የሴቶች ተሀድሶና ክህሎት ማጎልበቻ ማዕከል ተገኝተን ነገአቸው ብሩህ እንደሆነ እና አዲሱ ዓመት ወደ የበለጠ ለውጥ የሚመጡበት ዓመት እንደሚሆን ተመኝተን አብረናቸው ቆይታ አድርገናል።
በተጨማሪም ከህጻናት ጋር በነበረን ቆይታ በገነባናቸው የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች - በቀዳማይ ልጅነት ማዕከል፣ በወንድማማች 2 እንዲሁም በቦሌ የመደመር ትውልድ ሜዳ ላይ እንኳን አደረሳችሁ ብለን አብረናቸው አሳልፈናል።
የዛሬ ትጋት ለነገ ትሩፋት ብለን!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.