በሀገር ውስጥና በውጭ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ፤ እንኳን ለ2ዐ17 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።ከንቲባ አዳነች አቤቤ
በሰላም ያደረሰን ፈጣሪ አምላክ የተባረከና የተመሰገነ ይሁን። መልካም አዲስ አመት !
አዲሱን አመት የሠላም፣ የፍቅር፣ የደስታና የስኬት ያድርግልን፡፡
ባሳለፍነው ዓመት እንደ ሀገር የተጋረጡብንን በርካታ ፈተናዎች በድል የተሻገርንበት፣ ስኬታማ ስራዎችን በመስራት ውጤቶችን ያስመዘገብንብት፤ እና የሕዝባችንን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ያደርግናቸው ጥረቶች ፍሬ ማፍራት የጀመሩበት ነው፡፡
የኢትዮጵያ መልክ የሆነችው፡ መዲናችን አዲስ አበባም በፍቅር የደመቀች እና በህብረ-ብሔራዊነት ያጌጠች ከተማ መሆኗን በተግባር እያሳየች የአብሮነት፣ የመተባበርና የመከባበር እሴትን አጠናክራ ያሳየችበት አመት ነው፡፡
ባለፈ ያሳለፍነው አመት አብሮነታችንን በማጠናከርና የበጎ ተግባር ስራዎቻችንን በማስፋት፡ የበርካታ የከተማችንን አቅመ ደካማ የሀገር ባለውለታዎች እና ለችግር የተጋለጡ ወገኖችቻንን እንባ ያበስንብት፣ ትኩረትና ክብር ተነፍጓቸው የኖሩ ወገኖቻችንን ዝቅ ብለን በማገልገል ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ያጎላንበት አመትም ነው፡፡
ልማታችን ማንንም ወደኋላ የተወ አይደለም፡፡
በመሆኑም ባሳለፍነው ዓመት እንደ ሀገር ያስመዘገብናቸው የተሻሉ ውጤቶችን በመዘከር በቀጣይ ትልሞቻችን ላይ የሰላምና የልማት ሀይሎችን በማስተባበር በርካታ ሀገር አሻጋሪ ተግባራትን ለማከናወን ተዘጋጅተናል፡፡
በአዲሱ አመት እስከ አሁን በሰራነው ሳንረካ ይልቁንም የዛሬውን ትውልድ ከነገው ትውልድ ጋር በማስተሳሰር የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ በብዙ ጥረት፣ በብዙ ትጋትና እና በማያቋርጥ ልፋት እጅ ለእጅ ተያይዘን በመስራት ሕዝባችንን ዝቅ ብለን እናገለግላለን፡፡
አዲሱ ዓመት በአንድነት የምንነሳበት፤ ከማይረቡን አጀንዳዎች ርቀን፡ እጆቻችንን ለስራ በማትጋት የሀገራችንን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት በማረጋገት ሰላማችንን ምናፀናበት ከውጭና ከውስጥ የሚተናኰሉንን ሀይሎች በመመከት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት አስጠብቀን የምንቀጥልበት እንደዚሁም የነዋሪዎቻችንን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ለመመለስ ተግተን የምንሰራበት ፍሬያማ ዓመት እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ ፡፡
አመሰግናለሁ
መልካም አዲስ ዓመት!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.