በቀን አንዴ እንኳን መመገብ ለማይችሉ ወገኖቻችን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በቀን አንዴ እንኳን መመገብ ለማይችሉ ወገኖቻችን 21ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል የአዲስ ዓመት ስጦታችን አድርገን እነሆ ብለናል:: የረዳን ፈጣሪ ይመስገን!!ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በአዲስ ዓመት በቀን 1 ሺህ ሰዎችን የሚመግበውን 21ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተማ አየርጤና አካባቢ መርቀን በቀን አንዴ እንኳን መመገብ ለሚቸገሩ ወገኖቻችን መልካም አዲስ ዓመት ብለን ምገባ አስጀምረናል።

ከተማችንን ማህበራዊ ፍትህ የነገሰባት ለማድረግ ከጀመርናቸው ስራዎች አንዱ በቀን አንዴ እንኳን መመገብ የሚቸገሩ ወገኖቻችንን መመገብ ሲሆን 21ኛውን የምገባ ማዕከል በረከት ገበሬዋ ገንብታ አስረክባናለች።

በቀጣይም ሙሉ ወጪውን ችላ 22ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ገንብታ ለወገኖቿ ለማስረከብ ቃል የገባችልን ሲሆን፣ ለበጎነቷ በተጠቃሚ ነዋሪዎቹ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ላመሰግናት እወዳለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.