ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን የሰጡንን የስራ መመሪ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን የሰጡንን የስራ መመሪያ ተቀብለን በቢሾፍቱ ከተማ በመገኘት የኮሪደር ልማት ስራ ያለበትን ደረጃ ጎብኝተናል።ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከከተማዉ አመራሮች፣ አባገዳዎች ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ ሀደ ስንቄዎች እንዲሁም ከነዋሪ ተወካዮች ጋር በተያዙ እቅዶች እና በቅንጅት በምሰራበት አግባብ ዙሪያ ተወያይተናል።

በቢሾፍቱ ከተማ የተጀመረው የኮሪደር ልማት ስራ በአምስት አካባቢዎች ሰፊ በሆነ ቦታ ላይ የሚከናወን ሲሆን በውስጡም የመንገድ ስራ፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገድ ስራ፣ የህዝብ መዝናኛ ፓርክ እንዲሁም መንገዶችን የማስዋብ ስራን ያካተተ ነው።

በእርግጥ ቢሾፍቱ በተፈጥሮ የታደለች ከሰባት ሀይቆች በላይ ያላት የቱሪስት መዳረሻ ከተማ ናት። የኮሪደር ልማት ስራው ሲጠናቀቅ ይበልጥ የቱሪስት መስህብነቷን የሚጨምር ሲሆን የከተማዋን የወደፊት እድልም ከፍ የሚያደርግ ይሆናል።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.