በከተማ አስተዳደሩ የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በዛሬው እለት በይፋ ተጀመረ።
ትምህርቱ በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የተጀመረ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር በመሆን የመማር ማስተማር ሂደቱን በድምቀት አስጀምረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የቢሮ ኃላፊ ተወካይ ወይዘሮ ታጋይቱ አባቡ በዳግማዊ ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ትምህርቱን ባስጀመሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ አጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እንኳን በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በ2017 ዓ.ም የትምህርት አመት በ2016 ዓ.ም የነበሩንን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ምክትል ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም በ2017 ዓ.ም የትምህርት አመት ተማሪዎች ለትምህርት አገልግሎት ከሚጠቀሙባቸው የመማሪያ ቁሳቁሶች ባሻገር የሞባይል ስልኮችን ጨምሮ ሌሎች የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው መምጣት እንደማይችሉ ጠቁመው ቢሮው በ2017 ዓ.ም የትምህርት አመት የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.