ኢትዮጵያ የካፍ ጠቅላላ ጉባዔን እንድታስተናግድ ተወሰነ
የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባደረገው ስብሰባ የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ እንዲካሄድ ወሰነ፡፡
ጉባዔው በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ እንዲካሄድ ታስቦ የነበረ ቢሆንም÷ ሀገሪቱ ማስተናገድ እንደማትችል ማሳወቋን ተከትሎ ኢትዮጵያ ጉባዔውን ለማካሄድ ያቀረበችውን ጥያቄ ካፍ አጽድቋል፡፡
በዚህም መሰረት የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ በጥቅምት ወር በአዲስ አበባ ከተማ እንደሚካሄድ መገለጹን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.