በዓላት በአብሮነትና በድምቀት እንዲከበሩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል - ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ
የአደባባይ በዓላት የቱሪስት መስህብ በመሆን ላቅ ያለ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳም አለው ተብሏል ።
ለአብነትም የመስቀል ደመራ እና የእሬቻ በዓላት ከሀይማኖታዊ እና ማህበራዊ ፋይዳቸው በተጨማሪ ዲያስፖራዎች እና በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች የሚሳተፉባቸው የሀገር ሀብት ናቸው::
በዓላት እሴቶቻቸው ተጠብቆ እንዲከበሩ እና የህዝባችንን ማህበራዊ መስተጋብር እንዲያጠናክሩ እንደ ፓርቲም እንደ መንግስትም የተጀማመሩ አበረታች ስራዎች ወንድማማችነት እና እህትማማችነት እንዲጠናከር አስችለዋል።
የበዓላት ሀይማኖታዊ ፣ ማህበራዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ለሀገረ መንግስት ግንባታውም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ በጀመርነው አዲስ ዓመትም ቅንጅታዊ ርብርቡ ይጠናክራል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ የመስቀል ደመራን እና የእሬቻ በዓላትን በሰላምና በድምቀት ለማክበር እየተደረጉ ያሉ ቅድመ ዝግጅቶችን ከባለድርሻ አካላት ጋር ገምግሟል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በውይይቱ ላይ እንደተናገሩት የመስቀል ደመራ እና የእሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸው ተጠብቆ በሰላም እንዲከበሩ የፀጥታ አካላት እና ባለድርሻ አካላት ተገቢውን ቅድመ ዝግጅቶን እያደረጉ እንደሚገኙ ገልፀዋል።
ሁሉም አካባቢውች ከስጋት የራቁ ሰላማዊ ሆነው እንዲዘልቁ ቅንጅታዊ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ያሉት ወ/ሮ ሊዲያ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በዓላት በአብሮነትና በድምቀት እንዲከበሩ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በዓሉ ወንድማማችነትን እህትማማችነትን እና አብሮነትን በሚያጠናክር መልኩ በድምቀት እንዲከበር የፀጥታ መዋቅሩ እስከ ብሎክ ከሚገኘው የሰላም ሰራዊት እና ከሁሉም ህብረተሰብ ጋር ተቀናጅቶ ለመስራት በቂ ዝግጅት እያደረጉ እንደሚገኙ ክፍለ ከተሞችም አረጋግጠዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.