በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ፤ ባለሙያዎች እና ደላሎች በሙስና ወንጅል ተጠርጥረዉ በቁጥጥር ሥር ዋሉ::
ለከንቲባ ጽ/ቤት በደረሰ ጥቆማ መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ የሆኑት 1ኛ. አቶ ሃብታሙ ግዲሳ ጆቴ 2ኛ. ስምረት ገ/እግዚአብሔር አሰፋ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 3ኛ. አቶ ዮሴፍ ባቡ ሆራ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 4ኛ. አቶ አቤኔዘር ቶሎሳ ሙሉ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር 5ኛ. አቶ ለሚ ሲሌ ከፍተኛ ግብር ከፋይ የታክስ ኦዲት ከፍተኛ ኦፊሰር እና 6ኛ. ወ/ሮ መቅደስ አረጋዊ ገንዘብ ተቀባይ የሆኑት በቀን 06/01/2017 ዓ.ም በሙስና ወንጅል ተጠርጥረዉ በቁጥጥር ስር ውለዉ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል::
ከ1ኛ እስከ 5ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት ተጠርጣሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የታክስ ኦዲት ቡድን አስተባባሪ፤ ባለሙያዎች ሲሆኑ ጳጉሜ 05/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ውስጥ ግብር ከፋይ ከሆኑ ግለሰብ የ2011 ዓ.ም እና 2012 ዓ.ም የአንድ አመት ግብር ኦዲት እንዲደረግላቸዉ የሚጠበቅበትን ሰነድ ያቀረበላቸዉ ሲሆን መክፈል ያለብህ አንድ መቶ ሚሊየን ብር (100,000000) ነዉ በማለት የገለፁለት በመሆኑ፤ ይህን ያህል አልከፍልም ካልክ ግማሹን አስይዘህ ነዉ ይግባኝ የምታቀርበዉ በማለት ያቀረቡ ሲሆን ፤ ለጊዜዉ በቁጥጥር ስር ያልዋለ ግለሰብ ሂሳብ አስጨራሽ በሚል የቀረ ደላላ ጉዳዩን አስተካክላለሁ በሚል በማግባባት ለራሱ ሶስት ሚሊየን ብር (3,000,000) እና ለሰራተኞቹ ስምንት ሚሊየን ብር (8,000,000) ለመንግስት ከመቶ ሚሊየን በመቀነስ አስራ ሶስት ሚለየን ብር (13,000000) ትከፍላለህ በማለት (8,000,000) ስምንት ሚሊየን ብር በቤተሰቦቻቸዉ በመቀበል 13, 000,000 (አስራ ሶስት ሚሊየን ) ብር የመንግስት የሚከፈለዉን እንዲከፍል መተማመኛ ሲሰጡት በተደረገ ክትትል እጅ ከፍንጅ የተያዙ እና ምርመራዉ ቀድሞ በነበረዉ ክትትል በስፋት እየተጣራ ይገኛል ፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.