225 የካሳንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺዎች የመንግስት መኖሪያ ቤት እጣ በዛሬው እለት አውጥተዋል፡
በዛሬው እለት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ የካዛንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺዎች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ቢሮ በመገኘት የመንግስት መኖሪያ ቤት እጣ አውጥተዋል፡፡
ባለ አንድ እና ባለ ሁለት መኝታ በአጠቃላይ 225 የመንግስት መኖሪያ ቤቶችን በአቃቂ፣ አራብሳ፣ገላን፣ ፈረንሳይ ጉራራ እና ጃርሶ ሳይት የመኖሪያ መንደሮች ለባለእድለኞች በእጣቸው መሰረት ተደራሽ አድርገናል ያሉት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ናሆም መንግስቱ ናቸው፡፡
ኃላፊው አክለውም ከዚህ ቀደም ለነዋሪዎቻችን ፍትሃዊ በሆነ እና በተሳካ መልኩ የኮንዶሚኒየም ቤት እጣ የማውጣት ስነ-ስርዓት አካሄደናል የዛሬውም በተመሳሳይ መልኩ ካለምንም ችግር ማከናወን ችለናል ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በልማቱ ተነስተው በተለያዩ አካባቢዎች የመኖሪያ ቤት የተሰጣቸውን ነዋሪዎቻችን ሄደን ጎብኝተናል ያሉት ደግሞ የወረዳ 08 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ብርሀኑ ሀይሉ በዚህ እጣም በተመሳሳይ ነዋሪዎቹ ካላቸው የጋራ የኑሮ ዘይቤ ላለመለየት በአንድ አካባቢ እንዲሆኑ ጥረት ተደርጓል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም የልማቱ ተነሺዎች ማንኛውም አይነት ቅሬታ ካለቸው በአካል በመቅረብ ማሳወቅ እንደሚችሉ በመግለጽ ለልማቱ መሳካት ቀናነትን በመላበስ ከጎናችን በመቆማቸሁ ምስጋና ይገባችኋል ብለዋል፡፡
የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ዛሬን ጨምሮ በቀጣይም እንደሚቀጥል ተገልጿል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.