የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓል የአብሮነት የወንድማማችነት/ የእትማማችነት የፍቅር መገለጫ ስለሆኑ በጋራ እናከብራለን።
የልደታ ክፍለ ከተማ 2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻ በዓል ያለምንም ፀጥታ ስጋት እንዲከበር ከነዋሪዎች ጋር ውይይት ተደረገ።
የውይይት መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ ምክትል ቢሮ ሀላፊ መላኩ ታምሩ በቀጣይ የሚከበሩ የአደባባይ በዓላት በሰላም በወዳጅነት እንዲ ሀይማኖታዊ ባህላዊ የምናጠናክርበትና ሰላምን የምናፀናበት በመሆኑ ሁሉም ነዋሪ ባለቤት ሊሆን ይገባል ብለዋል።
አቶ መላኩ አክለው ለመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበር የተከለከሉና ለግጭት መነሻ የሚሆኑ ነገሮችን በማስቀረት የክፍለ ከተማ ፀጥታ ተጠብቆ በዓሉ እንዲከበር ከሁሉም ነዋሪ ጋር በቅንጅት መስራት ይገባል በማለት ገልፀዋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይ ዶ/ር ጥበቡ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓል የአደባባይ ስናከብር ያለምንም ፀጥታ ስጋት የፍቅርና የአንድነት የመተሳሰብ እሴቶቻችንን ጠብቀን ማሳለፍ ይጠበቅብናል በማለት ገልፀዋል።
ዶ/ር ጥበቡ አክለው ሁሉም አመራርና አደረጃጀት በቀጠና በብሎክ ስምሪት በመውሰድ በቀጣይ የምናከብራቸው በዓላት ወጉን ቱፊቱን ጠብቆ እንዲከበር የድርሻውን ሊወጣ ይገባል በማለት ገልፀዋል ።
የልደታ ክ/ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካን አቶ ስንታየሁ ተረፈ እንደገለፁት በአደባባይ የሚከበሩት የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት ጥላቻን በማስወገድ አንድነትን ፣ፍቅርን ፣መደጋገፍን ፣መረዳዳትን መሠረት በማድረግ በሰላም ማክበር ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ይጠበቃል ብለዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በዓላቱ በአደባባይ የሚከበሩ በመሆኑ ጎብኚዎች ወደ ሀገራችን በመምጣት አብረውን የሚያከብሩ ስለሆነ በቅንጅትና በትብብር በሠላም እናከብራለን ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.