መጪው የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት አከባበር ዙሪያ ከአጎራባች የሸገር ከተማ ነዋሪዎች ጋር የህዝብ ለህዝብ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር መጪዎቹ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት በሰላም አከባበር ዙሪያ ከአጎራባች የሸገር ከተማ የኮዬ ፈጬ ክ/ከተማ ፣ የገላን ክ/ከተማ እና አጎራባች ወረዳዎች ነዋሪዎች ጋር የህዝብ ለህዝብ የውይይት መድረክ አካሂዷል ።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈይሳ ፈለቀ፣ የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ መሀመድ አህመድና የክ/ከተማው ዋና አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ሙሉጌታ አሰፋ ፣ የአጎራባች ክ/ከተማ አመራሮችና ነዋሪዎች ፣ አባገዳዎች ፣ ሀደ ሲንቄዎች ፣ ወጣቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን ለውይይት መነሻ የሚሆን ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በዓላቱ የሁሉም ኢትዮጵያውያን መገለጫ የሆኑ የሰላም በዓላት መሆናቸውን በማንሳት በዓላቶቹ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበሩ አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ ከፀጥታ ሃይሎች ጋር በመቀናጀትና በመተባበር አንድነትንና አብሮነታችንን በሚያጠናክር መልኩ እናከብራለን ሲሉ ተናግረዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈይሳ ፈለቀ እንደገለፁት በዓላቱ የፍቅር የሰላም የወንድማማችነትና የአብሮነት መገለጫ በመሆናቸው በዓሉን ለማጠልሸት የሚጥሩ አካላትን አጋልጦ በመስጠት በዓላቱ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበሩ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወካይና የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ መሀመድ አህመድ ክ/ከተሞቹ ምንም እንኳን በወሰን ቢለያዩም በሰላምና በልማት ጉዳዮች በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙ በመግለፅ መጪው በዓላት ሀይማኖታዊ ስርዓታቸውንና ባህላዊ ትውፊታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ በቅንጅትና በትብብር መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.