203 የካሳንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺ ነዋሪዎች የመንግስት መኖሪያ ቤት እጣ በዛሬው እለት አውጥተዋል
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የካዛንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺ ነዋሪዎች የመንግስት መኖሪያ ቤት እጣ የማውጣት ስነ ስርዓቱ እንደቀጠለ ነው፡፡
በአጠቃላይ በ3 ቀናት ውስጥ የዛሬውን ጨምሮ 428 የልማት ተነሺ የካሳንቺስ ነዋሪዎች የመንግስት መኖሪያ ቤት እጣ በማውጣት ቤታቸውን እየተረከቡ ይገኛሉ።
ባለ አንድ እና ባለ ሁለት መኝታ የመንግስት መኖሪያ ቤቶችን በአቃቂ፣ አራብሳ፣ገላን፣ ፈረንሳይ ጉራራ እና ጃርሶ ሳይት የመኖሪያ መንደሮች ለባለእድለኞች በእጣቸው መሰረት ተደራሽ እየተደረገ ነው።
የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ነገን ጨምሮ በቀጣይ ቀናትም እንደሚቀጥል ተገልጿል።
የልማቱ ተነሺዎች ማንኛውም አይነት ቅሬታ ካለቸው በክፍለ ከተማው አስተዳደር 10ኛ ፎቅ ወደተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በአካል በመቅረብ ወይም በ9065 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉም ተገልጿል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.