በከተማችን ያለውን አስተማማኝ ሰላም ዘላቂ እንዲ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

በከተማችን ያለውን አስተማማኝ ሰላም ዘላቂ እንዲሆን የሰላም ደጀን ብቻ ሳይሆን ዋናው ባለቤት የሆነው ህዝባችን ህፃን አዋቂ፣ ሴት ወንድ፣ ወጣት አዛውንት ሳይል አካባቢውን 24 ሰዓት በንቃት እየጠበቀ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ባስተላለፍት መልዕክት የአብሮነትና የፍቅር መገለጫ የሆኑት የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት በሰላም እንዲጠናቀቁ ለሰላም ሰራዊት በአንድ ማዕከል እየተሰጠ ያለው ስምሪት የሚበረታታ ነው ብለው ስምሪቱ በቀጣይም ተጠናክሮ ቀጥሎ በዓላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁ ማድረግ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማዋ "ሁሉም ለሰላም ሰላም ለሁሉም" በሚል መርህ ማህበረሰቡን ያሳተፈ የሰላም ማስፈን ተግባር ማከናወን ከጀመረ ጊዜ አንስቶ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ወ/ሮ ሊዲያ ገልፀው፥ የአንድነት የወንድማማችነት የእህትማማችነት የመከባበርና የሰላም ተምሳሌት የሆኑት የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ሀይማኖታዊና ታሪካዊ ቱፊታቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲጠናቀቁ ለማስቻል የሰላም ሰራዊቱ ከፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በትጋት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ሰላምን ማስጠበቅ ተቀዳሚ ተግባራችን ነው ያሉት ስምሪት የወሰዱት የሰላም ሰራዊት አባላት ዛሬም ሆነ ነገ ለሰላም መከበር በትጋት እንሰራለን ብለዋል።

የሰላም አርበኛው ህዝባችን የሰላም ባለቤት እኔ ነኝ በማለት ለአካባቢውና ለከተማችን የሰላም ዘብ ሆኖ በየሰፈሩ የሚፈፀሙ ህገወጥ ድርጊቶችንና ማንኛውንም ወንጀል አስቀድሞ ይከላከላል፤ ወንጀል ፈፃሚዎችንም ለፀጥታ አካላት በመስጠት የህግ የበላይነትን ያሰፍናል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.