በመጭው ቀናት የሚከበሩት የመስቀል፣ ደመራና ኢሬቻ በዓላት በወንድማማችነት እና እህትማማችነት መንፈስ ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ የበኩላችንን እንወጣለን ሲሉ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ተናገሩ::
በአዲስ አበባ ከተማ በመጭው ቀናት የሚከበሩትን የመስቀል፣ ደመራና ኢሬቻ በዓላት ኃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ የሚያስችል ህዝባዊ ውይይት በዛሬው እለት በ11ዱም ክፍለ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በውይይቱ ላይ የተለያዩ የህብረተስብ ክፍሎች የተሳተፉ ሲሆን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መከናወኑ እንዲሁም ህዝባዊ ውይይት መከያሄዱ በአላቱን በሰላም ፣በአንድነት በህብረት ባማረ መልኩ ለማሳለፍ ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
በዓላት በዩኔስኮ የአለም ቅርስነት የተመዘገቡ መሆናቸው ከኃይማኖታዊና ባህላዊ ስርዓት ከማሻገር በተጨማሪ ከተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚመጡ ጎብኝዎ ስለሚታደሙ የሀገር ገፅታ ከፍ ከማድረግ ባሻገር ትልቅ የቱሪዝም ገቢ በማስገኘት ከፍተኛ ፋይዳ ስለሚኖራቸው በአብሮነት ስሜት ሊከበሩ እንደሚገባ ተጠቁሟል።
የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት አዲስ አበባ ከተማ እንግዶቿን ተቀብላ ለማስተናገድ የተለያዩ የቅደመ ዝግጅት ስራው ከወዲሁ በማድረግ ላይ እንደምትገኝ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.