መጪዎቹን የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላትን...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

መጪዎቹን የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላትን በሰላም እንዲከበሩ በሚደረገው ቅድም ዝግጅት ዙሪያ የቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ውይይት ተካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሚኪያስ ሙሉጌታ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት የኢትዮጵያ መገለጫ እንዲሁም ሃይማኖታዊና ባሕላዊ እሴቶች እንደሆኑ ገልጸው፣ "መዲናችን አዲስ አበባ እነዚህን በዓላት በድምቀትና ሰላማዊ በሆነ መንገድ በክብር ያላትን ተመክሮ ዘንድሮም በበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል የነዋሪዎቿ ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።

 በዓላቱ ያለምንም የጸጥታ ሥጋት እንዲከበሩ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ያመለከቱት አቶ ሚኪያስ፣ የቦሌ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች በተለመደው እንግዳ ተቀባይነትና ሰላማዊነት ለበዓላቱ ስኬታማነት የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደሰ በሪሶ የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት የሰላም፣ የእርቅ እና የምስጋና በዓላት መሆናቸውን አውስተው፣ እነዚህ በዓላት እሴታቸውን በጠበቀ መልኩ እንዲከበሩና ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን እኩይ ሴራ ለማክሸፍ የክፍለ ከተማው ነዋሪዎችየተለመደ አጋርነታቸውን ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል። 

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ሰላም ያለሕዝብ ተሳትፎ እንደማይረጋገጥ ገልጸው፣ ይህንን ለማሳካት በመጪዎቹ በዓላት ለሰላም ዘብ በመቆም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.