በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 እና ወረዳ 07 አስተዳደር በመገኘት የሰላም ሰራዊት አባላትን አበረታቱ።
የመስቀል ደመራና ኢሬቻ በዓላት ሐይማኖታዊና ባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ እንዲከበሩ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ የሰላም ሰራዊት አባላት እና የጸጥታ አካላትን በማቀናጀት እየተሰሩ ያሉትን የለሊት የአካባቢ ጥበቃ ስራ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ም/ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድርን ጨምሮ ሌሎች የከተማ ፣ የክፍለ ከተማ እና የሁለቱም ወረዳ አስተዳደር አመራሮች በወረዳ 05 እና 07 አስተዳደር
የአንድ ማዕከል ስምሪት ላይ በመገኘት ሰራዊቱን አበረታተዋል።
የሰላም ሰራዊት አባላት ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ተቀናጅተው በመስራታቸው በከተማችን ታላላቅ የአደባባይ በዓላት ያለአንዳች የፀጥታ ችግር ማክበር ችለናል ያሉት የቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ከፊታችን ባሉ ቀናት የምናከብራቸው የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት በተሳካ ሁኔታ በድምቀት እንዲከበሩ በክ/ከተማው የሰላም ሰራዊትን እና የጸጥታ አካላትን በማቀናጀት እየተሰራ ያለው የሰላም ማስከበር ስራ የሚደነቅ ነው ብለዋል።
የሰላም አርበኛው ህዝባችን የሰላም ባለቤት እኔ ነኝ በማለት ለአካባቢውና ለከተማችን የሰላም ዘብ ሆኖ በየሰፈሩ የሚፈፀሙ ህገ-ወጥ ድርጊቶችንና ማንኛውንም ወንጀል አስቀድሞ በመከላከል ወንጀል ፈፃሚዎችንም ለፀጥታ አካላት አሳልፎ በመስጠት የህግ የበላይነትን እንዲሰፍን እየተሰራው ያለው ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.