የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክፍለ ከ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልደታ ክፍለ ከተማ የመሬት ልማት ጽ/ቤት ተወካይ ሃላፊ የነበሩት አቶ ቴዎድሮስ ፀጋዬ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ሲፈለጉ የነበሩት በዛሬው ዕለት በእስካይ ላይት ሆቴል በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ተጠርጣሪው በኮሪደር ልማት ሽፍን በማድረግ ከመንግስት አሰራር እና ውሳኔ ውጪ በመደራደር ባልተገባ መንገድ ለግል ጥቅም ለማግኘት ሲል የካሳ ግምት በማናር ውስን የሆነዉን የህዝብ ና የመንግስትን መሬት ከአሰራር ውጪ በማሰተላለፍ ለግለሰቦች አላስፈላጊ ጥቅም በማዋል ፤ ተጠርጥረው በዛሬው ዕለት ከተሸሸጉበት እስካይ ላይት ሆቴል በቁጥጥር ሰር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪ ከሀገር ውጪ ወተዋል በማስባል የህግ ማስከበሩን እንዲስተጓል በማድረግ በዛሬው ዕለት በቁጥጥር ስር ውለዋል::

በተጨማሪም በክ/ከተማው ወረዳ 4 ዉስጥ በኮሪደር ልማት ኘላን ልማት ውስጥ የማይካተት ከመመሪያ እና አሠራር ዉጪ 6 መኖሪያ እና አንድ የንግድ ቤት የሆነውን ከዋይልድ አፓርትመንት የተባለ ህንፃ ባለቤት ጋር ተመሳጥረው ቤቶቹን እንዲፈርሱ በማድረግ እና ለህንፃው ማስፋፊያ እንዲሆን የሰጡ እና የመንግስት ቤት ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ግለሰቦች የእቃ የማጓጓዥያ ሳይከፈል እንዲነሱ በማድረጉ እንዲሁም ምትክ ቦታ እስጣቿለው በማለት አንደኛ ቦታ አስቀይርላቿለው ና የተለያዩ የማጭበርበር ወንጀሎችን በማድረግ ህብረተሰቡ ሲያደናግር ና ያልተገቡ ጥቅሞችን ሲያደርግ እንደነበረ የአዲስ አበባ የፀረ ሙስና ግብረ ሃይል አስታውቋል::


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.