የካሳንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺ ነዋሪዎች 34...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የካሳንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺ ነዋሪዎች 349 የመኖሪያ ቤት እጣ በዛሬው እለት አውጥተዋል፡:

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የካዛንቺስ አካባቢ የልማት ተነሺ ነዋሪዎች ተለዋጭ የመኖሪያ ቤት እጣ የማውጣት ስነ ስርዓቱ እንደቀጠለ ነው፡፡

በአጠቃላይ ባለፉት 6 ቀናት ብቻ 838 ነዋሪዎች ተለዋጭ የመኖሪያ ቤት እጣ በማውጣት ቤታቸውን እየተረከቡ መሆኑ ተገልጿል።

የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓቱ ዛሬን ጨምሮ በቀጣይ ቀናትም እንደሚቀጥል ተገልጿል።

 የልማቱ ተነሺዎች ማንኛውም አይነት ቅሬታ ካለቸው ከባንቢስ ወደ ደንበል በሚወስደው የቤቶች ኮርፖሬሽን ወይም በክፍለ ከተማው አስተዳደር 10ኛ ፎቅ ወደተቋቋመው የቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ በአካል በመቅረብ ወይም በ9065 ነፃ የስልክ መስመር በመደወል ቅሬታቸውን ማቅረብ እንደሚችሉም አስተዳደሩ ይገልጻል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.