አስተማማኝ ሰላማችንን አፅንተን ዘላቂ ለማድረግ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

አስተማማኝ ሰላማችንን አፅንተን ዘላቂ ለማድረግ ከፀጥታ መዋቅሩ ባሻገር ህዝባችን የሰላምና ፀጥታ ባለቤትነቱን ሊያጠናክር ይገባዋል - ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ

ህዝባዊ እና ሀይማኖታዊ በዓላት እሴቶቻቸው ተጠብቆ እንዲከበሩ እና ህብረብሔራዊ አብሮነትን እንዲያጠናክሩም 

በየአካባቢው የሚገኙ የሰላም ሰራዊት አባላት ሚና ላቅ ያለ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ከሰላም ሰራዊት ተወካዮች ጋር በተደረገው ከተማ አቀፍ መድረክ ላይ እንደተናገሩት የሰላም ሰራዊቱን አቅም በማጎልበት በተቋማዊ አቅም እንዲመራ ባለፈው ዓመት በንድፈ ሀሳብ ፣ በተግባር ስምሪት እንዲሁም ግብአቶችን ለማሟላት አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል።

ባለፈው ዓመት በከተማችን የተከበሩ የአደባባይ በዓላት በሰላምና በድምቀት እንዲከበሩ የሰላም ሰራዊቱ የላቀ አስተዋጽዖ ማበርከቱን የጠቆሙት ወ/ሮ ሊዲያ የዓለም ቅርስ ሆኖ በዩኔስኮ የተመዘገበው የመስቀል ደመራ በዓል እና የፍቅርና የአንድነት መገለጫ የሆነው የእሬቻ በዓል ዘንድሮም በተሻለ ድምቀት እንዲከበሩ አይነትና ቅርፃቸውን የሚለዋውጡ የወንጀል ድርጊቶችንና የአፍራሽ ሀይሎችን ሰላምን የማደፍረስ ሙከራ እንደተለመደው ከፀጥታ ሀይሉ ጋር ተቀናጅተው በማክሸፍ ዘላቂ ሰላምን እንዲያስቀጥሉ አስገንዝበዋል።

ከበዓላቱ ጋር ተያይዞ እሳትና መሰል ድንገተኛ አደጋዎችም እንዳይከሰቱ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ያስረዱት ሀላፊዋ የህዝብ ሀብት የወጣባቸውና የከተማችንን ገፅታ በእጅጉ የቀየሩ መሰረተ ልማቶችንም በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባ አመላክተዋል።

አስተማማኝ ሰላማችን አፅንተን ዘላቂ ለማድረግ ከፀጥታ መዋቅሩ ባሻገር ህዝባችን የሰላምና ፀጥታ ባለቤትነቱን ሊያጠናክር እንደሚገባ ያስገነዘቡት ሀላፊዋ የሰላም ሰራዊቱ በሶስት ፈረቃ አካባቢውን ተደራጅቶ ለመጠበት የጀመረውን ጥረት ማጠናከር እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ሚዴቅሳ ከበደ በበኩላቸው ህዝባችን ከፀጥታ ሀይሉ ጋር ተቀናጅቶ ሰላሙን በማስጠበቁ ከተማችን እንደ ስሟ እያበበች መሆኑን ማረጋገጥ ችሏል ብለዋል::

የፀጥታ መዋቅሩ ፣ ህዝባችንና ከእሱ የወጣው ለከተማችን ሰላም ዘብ የቆመው የሰላም አንባሳደሩ የሰላም ሰራዊት የመስቀል ደመራ እና የእሬቻ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውንም አቶ ሚዴቅሳ አስገንዝበዋል ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.