የ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ያለምንም...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል - ጥምር የፀጥታ ሃይል

የ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን ጥምር የፀጥታ ሃይሉ አስታውቋል።

የፀጥታ አካላቱ ለሚያከናውናቸው ተግባራት በተዘጋጀው የማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ እንደገለፁት፣ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ በሚያስችል አስተማማኝ ብቃት ሰፊ ዝግጅት ተደርጓል።

ከሐይማኖቱ አባቶችና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ጥምር የጸጥታ ሀይሉ በትኩረት እየሰራ ይገኛልም ብለዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በበኩላቸው፣ የመስቀል ደመራ በዓል ያለምንም የጸጥታ ስጋት እንዲከበር በየደረጃው ከሚገኙ የአስተዳደር አካላት ፣ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የሃይማኖት አባቶች፣ ከወጣቶችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይቶች መካሄዳቸውን ተናግረዋል።

በፀጥታ ስራው ላይ ህዝባዊ ንቅናቄ በመፍጠር የሽብር እና የፀረ ሰላም ሀይሎችን እንቅስቃሴ መቆጣጠር የሚያስችል የቅድመ መከላከል ስራ እየተሰራ መሆኑን በማስታወስ በዓሉ ሃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ያለ ምንም የፀጥታ ስጋት በድምቀት እንዲከበር ጥምር የፀጥታ ሃይሉን በመደገፍ በኩል ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በመድረኩ ባነሱት ሃሳብ ፣ ህብረተሰቡን እና በከተማዋ የሚገኙ መላው የሰላም ሰራዊት አባላትን በማሳተፍ የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲከበር የሚያስችሉ ስራዎች በተቀናጀ እና በተደራጀ መልኩ እየተሰሩ መሆናቸውን መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.