የ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራና የእሬቻ በዓላት ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብረው እንዲ ያልፍ በከተማ ደረጃ ውይይት ተካሄደ።
ውይይቱን የመሩት የትምህርት ጥራት እና ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ሃላፊ አቶ አዳማሱ ደቻሳ እስካሁን ባለን ታሪክ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን ፊትለፊት ገጥመው ያሸነፉበት ታሪክ የለንም የሀፍረት ሸማ አልብሰን የመሸኘት እንጂ ስለዚሀ በአሁኑ ጊዜም የውጪም ሆኑ የአገር ውስጥ ጠላቶቻችን የማሳፈር እና የአገርን ሉዓላዊነትና አንድነት ጠብቀን ለትውልድ የማሻገር ታሪካዊ ኃላፊነት አለብን ብለዋል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ /ፅ /ቤት የስልጠና እና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ጀማል መሀመድ በበኩላቸው የውይይቱ አስፈላጊነት፣ የዘንድሮው በዓል ከወትሮው አከባበር ለየት የሚያደርጉት ዋና ዋና ጉዳዮች የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሳይንስና ባህል ማዕከል በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገቡ በዓላት እንደመሆኑ መጠን ዓለማቀፍ ትኩረት ያላቸው በዓላት ናቸው ካሉ በኃላ እነዚህ በዓላት እሴታቸውንና ትውፊታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ለማድረግ ሁላችንም የድርሻችንን እንውጣ ብለዋል።
አቶ ጀማል አክለውም በዓላቱን በሰላም ለማክበር ከአጎራባች የሸገር ሲቲ ከተሞች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመው በዓላቱ የተጣሉት የሚታረቁበት፤ቂም በቀል የሚቀርበት እና ወንድማማችነት የሚነግስበት እንዲሆን መሥራት ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ል ሃላፊ አቶ ሚደቅሳ ከበደ እንደተናገሩት የውስጥና የውጭ ጠላቶች በዓላቱ በሰላም እንዲከበሩ የማይፈልጉ በመሆኑ ፍላጎታቸው እንዳይሳካ በማጋለጥ ለህግ አሳልፈን መስጠት እንዲሁም በዓላቱ የፖለቲካ ማራመጃ እንዳይሆኑ በፍቅር ፋንታ ጥላቻን የሚሰብኩ የተለያዩ ጹሁፍች፤ህትመቶችና ግጭት ቀስቃሽ ይዘት ያላቸው መልዕክቶች እንዳይተላለፉ ህብረተሰቡ የፀጥታ ኃይሎችን ማገዝ፤መተባበር ይኖርበታል ብለዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.