የመስቀል ደመራ ክብረ-በዓል በሁሉም ረገድ አብሮ...

image description
- ውስጥ Current Affairs    0

የመስቀል ደመራ ክብረ-በዓል በሁሉም ረገድ አብሮነትና ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትን አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ ሊከበር እንደሚገባ ተገለጸ

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ፤የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፣- የኃይማኖት አባቶች የመስቀል ደመረ በዓል በሁሉም ረገድ አብሮነትን አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ እንዲከበር የሚያስችል ውይይት አድርገዋል።

በውይይት መረሀ-ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ልድያ ግርማ እንዳሉት :-እንደቤተክርስቲያንቱ አስተምህሮ መስቀል ሰላም፣እርቅና ፍቅር ከሰው ልጆች ጋር የተፈጸመበት እንደመሆኑ ሁሉ በሁሉም አድባራት፣ገዳማትና በማክበሪያ አደባባዮች በዓሉ አብሮነትና ወንድማማችነትን አጉልቶ በሚያሳይ መልኩ ልከበር ይገባል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በበኩላቸው:- ከዚህ ቀደም በከተማዋ ስናደርግ እንደነበረው ሁሉ ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት የጸጥታ ስጋቶችን አስቀድመን በመከላከል፤ በዓሉ በላቀ አብሮነትና ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነት እንዲከበር የየድርሻችንን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል።

በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ፣ኢትዮጵያ ወንድማማችነትና አብሮነትን በማጽናት የሀገራችንን በጎ ገጽታ አጉልተን ለዓለም በማሳየት የመስቀል ደመራን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አሟጠን ልንጠቀም ይገባልም ያሉት የአዲስ አበባ የኃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጻፊ መጋቢ ታምራት አበጋዝ ናቸው።

ለዘመናት ጠብቀን ያቆየነውን አብሮነትና የኢትዮጵያዊ ወንድማማችነት ለመሸርሸር ተልዕኮ ወስደው የሚንቀሳቀሱ ሰርጎ-ገቦች አይኖሩም ማለት ስለማይቻል ፤የቤተክርስቲያቱ አባቶች በየደረጃው የደርሻችንን ኃላፊነት በአግባቡ እንወጣለን ያሉት ደግሞ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ፓፓስ፤ የተዋህዶ ሚዲያ የበላይ ኃላፊ፤የአዲሳ አበባ ከተማ የኃይማኖት ተቋማት ሰብሳቢና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ናቸወ።


Comments

ምንም አልተገኘም.

አስተያየቶችዎን ይተዉት.