መጪው የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻ በአላት በአብሮነትና በወንድማማችነት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር እንደሚሰሩ የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማና ሸገር ከተማ አስተዳደር የመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች ገለፁ።
ከሁለቱም ክፍለ ከተማዎች የተወጣጡ ወጣቶች በተገኙበት የመስቀል ደመራ እና ኢሬቻ በአላት አከባበር ዙሪያ የፓናል ውይይት ተካሒዷል።
የክፍለ ከተማው ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አቶ ሚኪያስ ገበየሁ አማካኝነት ባቀረቡት የመወያያ ሰነድ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በአላት የአብሮነትን፣ ወንድማማችነትን እና ሀገራዊ አንድነትን በሚያጎለብትና ለሀገር ግንባታ በሚረዳ መልኩ በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር በሁለቱ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ወጣቶች ሰላምን በማረጋገጥ ሰፊ ስራ መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።
ውይይቱን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ምክትል ስራ አስፈፃሚና የክፍለ ከተማው ደጋፊ አመራር አቶ ባዩ ሽጉጤ እንዳሉት በአሉ ሰላማዊ በሆኖና የህዝብ አንድነት ባረጋገጠ መልኩ እንዳይከበር የፀረ ሰላም ሀይሎች እንቅስቃሴን ሊኖር ስለሚችል ይህንን ወጣቶች በንቃት በመከታተል ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ለሰላም መስራት ይገባቸዋል ብለዋል።
ሁለቱም በአላት የኢትዮጵያዊያን በአል ናቸው በበአሉ የተፈቀዱና የተከለከሉ ጉዳዮች አሉ እነዚህን ጉዳዮች ወጣቶች በትክክል እንዲተገበሩ እንዲሁም ሌሎችን ማስገንዘብና መስራት ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።
የክፍለ ከተማው የዋና ስራ አስፈፃሚ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሰኢድ መሀመድ እንዳሉት መሰል ውይይቶች እንደሚቀጥሉ የገለፁ ሲሆን በአላቱን ፍፁም ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ ወጣቶች ሚናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።
የመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ የወጣቶችና ስፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሚደቅሳ ገለታ የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በአላት ፍፁም ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ ተደጋጋሚ ውይይቶችን ከኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ጋር መካሔዱን ገልፀው አሁንም በአላቱ ሰላማዊ ሆነው እንዳይከበሩ የሚሰሩ ፅንፈኞችን የማጋለጥ እና ለህግ የማቅረብ ስራ በጋራ ቅንጅት እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል።
የቀጣይም የሁለቱ ክፍለ ከተሞች የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አቶ ሚደቅሳ አስታውቀውቀዋል።
የፓናል ውይይት ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው በአላቱ ፍፁም ሰላማዊ ሆነው እንዲከበሩ ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰሩና በወንድማማችነት በአብሮነት ለማክበር መዘጋጀታቸውን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.