ማምሻውን ካዛንቺስ አካባቢ በኮሪደር ልማት መልሶ ማልማት የሚነሱ የተወሰኑ ተነሺዎችን ቤት ጎብኝተናል::
ከሚያማምሩ ፎቆች ጀርባ እጅግ በጣም አሳዛኝ እግር መዘርጊያ እንኳን የሌላቸው፣ በቆርቆሮ እና በሸራ የተለበዱ ያረጁ ፣ መፀዳጃና መኖሪያ ቤት የተቀላቀሉ ፣ መፀዳጃ የሌላቸዉ በቆጥ ላይ ሳይቀር የሚኖሩ እንዲሁም ማብሰያ ቦታ ሳይኖር የሚኖሩበት አስቸጋሪ እና ለመኖር ከባድ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን አይተናል::
እኛ ጎብኝተን ለመውጣት እንኳን አስቸጋሪ መሆኑን አየን እነሱ ግን ለረዥም አመታት እንደኖሩበት ስናስብ በእጅጉ አዝነናል::
ይህንን ሁኔታ ከመቀየር በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ምንም ስራ የለምና እንደተለመደው ሁሉ የከተማችን ነዋሪዎች ተባብረን ይህንን አካባቢ በመቀየር ለነዋሪዎችና ለኑሮ ምቹ እንድናደርግ ጥሪ አቀርባለሁ::
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
Comments
ምንም አልተገኘም.
አስተያየቶችዎን ይተዉት.